ስለ ኢትዮጵያኛ
ኢትዮጵያውያን ታላቅነት ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ ሳይሆኑ የሚናገሩት ታላላቅ የታሪክ ሰዎችና ቀደምት ፈላስፋዎች ጭምር ነቸው፡፡
ታላቁ የግርክ
ባለቅኔ ሆሜርስ ኢትዮጵያውያን ሃያላን በመልክ የተደነቁና የሚማርክ ውበት ያላቸው ናቸው፡ በባሕርያቸውም ጭምቶችና ትሕትናን
የተላበሱ ናቸው፤የ12ቱ የግሪክ አማልክተ አባት የሆነው ዜውስ የነዚህን ኃያላን ኢትዮጵያውያንን ውበት የማየት
አብሮም ለመብላት ወደ ውቅያኖስ ወረደ፡ ሲል ከክርስቶስ ልደት በፊት በ5ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን መጨረሻ አካባቢ የነበረው ታላቁ
የታሪክ አባት ሔሮዶቶስ ደግሞ በበኩሉ ኢትዮጵያውያን በቁመት፤በኃይልና በውበትም ከሁሉ የላቁ ናቸው በማለት መስክሯል፡፡
እንዲሁም ታላቁ የዓለም የሥነ-ጽሁፍ አባት ዊሊያም ሸክስፒር የጥቁርን ይልቁንም የኢትዮጵያዊን ውበት በታወቁት የፍቅር ግጥሞች
ስብስቦቹ ለዛን በተመሉ ማራኪ ስንኞች አስውቦ ገልጦታል፡፡
ታዲያ ይህ ሁሉ
ዓለም ያደነቀው ውበት የሥጋ ብቻ ሳይሆን የባህርይ ወይም የጠባይ፤ የእግዚአብሔር ጸጋና የመንፈሳዊነት ውበት ጭምር ነው፡፡
No comments:
Post a Comment