Ethiopia

Ethio by God/ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ዘንድ
"Ethiopia will stretch out her hands to God.." Psalm 67:31
ኢትዮጵያ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን ኩሽ የሚለውን 
የእብራይስጥ ቃል ነው ኢትዮጵያ ብለው ሰብአው ሊቃውንት የተረጎሙት፡ወደ አማርኛ ሲተነተን ጥቁር ወይም ጠይም ወደሚለው እንደሚያመዝን የቋንቋና የታሪክ ተመራማሪዎች ያትታሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ“ኢትዮጵያ” ወይም ኩሽ የሚለውን ሃይለ ቃል በምስጋና ብቻም ባይሆን በተግሣጽም ጭምር በ17የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 47ጊዜ  ጠቅሶት ይገኛል። 

በትንታኔውም ስለ ኢትዮጵያ የመልክአ ምድር ይዘት ፤ ስለ ሕዝቧ ባሕርይና እምነት ፤ እንዲሁም ሥልጣን ፤ መልክና ውበት ፤  ወዘተርፈ ያትታል ። በሌላ መልኩም ያለፉ 
ተግሣጻዊ ታሪኮችና እንዲሁም ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያዎችም አሉበት ። 

ኢትዮጵያ ሲባል አገሩን፤ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ሕዝቧን ማለት ሚሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያ እያለ የሚጠቅሰው ምሁራንም “ኢትዮጵያ ማለት ጠይም ወይም ጥቁር ማለት ነው፤ እያሉ የጥቁርን ውበት መጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አድርገው ሲያራቅቁ መሬቱን ወይም የኢትዮጵያን ወንዝና ሸንተረር ሳይሆን ሕዝቧን ማለታቸው መሆኑ የታወቀ ነው።

ኢትዮጵያ ማለት ጥቁር ወይም ጠይም ማለት እንደ ሆነ ከዚህ በላይ አትቻለሁ። ጥቁር ወይም ጠይም ደግሞ የተወደደ መልክ፤ውበትን የተላበሰ ቀለም እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ሳይቀሩ በአድናቆት ይገልጹታል፡፡ ጥበበኛው የኢየሩሳሌም ንጉሥ ሰሎሞን የመዝሙሮች ሁሉ መዝሙር (ከምስጋና ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን ምስጋና) እየተባለ በሚጠራው መዝሙሩ.
ጸላም አነ ወሰናይት እም አዋልደ-ኢየሩሳሌም” ማለትም እናንት የኢየሩሳሌም ቆነጃጅት ሆይ እኔ ጥቁር ነኝ ነገር ግን ውብ ነኝ እንደቄዳር ድንኳኖች፣እንደሰሎሞንም መጋረጃዎች ጸሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለሆንኩ አትዩኝ፡ መኃ.1 5፡፡
በማለት የጥቁርን፤የጠይምን ወይም ኢትዮጵያዊን  መልክ ይገልጠዋል። ነጮች በጥቁሮች ይልቁንም በኢትዮጵያውያን የቆዳ ቀለም ይቀናሉ፡፡ አገራችን እትዮጵያ በሰዎችም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደች፤የተደነቀች፤የተመረጠችና ዝነኛም ናት፡፡

 ልጆችዋም ሥጋዊ ውበታቸው ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊው ውበታቸውም የተወደደ ነው፡፡በአስተዋይነታቸው በሰው አክባሪነታቸው፤ በእንግዳ በቀባይነታቸውና በሰው አፍቃሪነታቸው በአጠቃላይ በሥጋዊውም ሆነ በመንፈሳዊው ሕይወታቸው በዓለም ዙሪያ የተመሰከረላቸው የተወደዱ ናቸው፡፡
በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ወላጆቻችን ይሉኝታ የሌለው፤ትሕትናን የማያውቅ፤በዕድሜ የሚልቁትን አባቶቹንና እናቶቹን የማያከብር፤በአጠቃላይ ያልተስተካከለና ያልተገራ ጠባይን የሚያሳይ ሰው ሲያጋጥማቸው ኢትዮጵያዊ መልክ የሌለው ይሉታል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም አንስቶም አይጠግበው፡ ከ47 ጊዜ በላይ ደጋግሞ የሚጠራው ሲሆን በአብዛኛው ተጠቅሶ የሚገኘው እምነቷ፤ጀግንነቷ፤መልክኣ ምድሯና ለእግዚአብሔር ያላት ቅርበት ወዘተ--ነው፡፡

ከነዚህ መካከል ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ የተከበበች መሆኗን፤ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር እንደምትዘረጋና ኢትዮጵያውያንንም ሕዝቤ፣የበኩር ልጄ እያለ ከሚጠራቸው ከእሥራኤላውያን በላነሰ ፍቅር እንደሚወዳቸውና እንደሚወደን የእሥራዔል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን በማለት የተናገራቸው ዕፁብ ድንቅ ጥቅሶች ይገኙ በታል፡፡ ዘፍ.2 13፡፡ መዝ.67 31፡፡ አሞ.9 7፡፡



No comments:

Post a Comment