Sunday, June 15, 2014

The Grace of Ethiopia

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተለየ ፍቅር እንደሚወደን በቃል ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡ ከዓለም የተለየ ክብርና ታሪክ አጎናጽፎናል፡፡ ይህም በሚከተሉት ዓለም አቀፍ የታሪክና የእምነት ቅርሶች ሊገለጽ ይችላል፡፡ከነዚህም መካከለል
ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቶሎሣ እንደሌለ ያስተባበሉት ግን እውነት እውነት እንጂ ሌላ ስም ስለማይኖረው ትርፉ ትዝብት ይልቁንም ቅሌት ብቻ ነው፡፡

1ኛ. ከዓለም የተሰወረው በእግዚአብሔር ጣቶች 10ሩ ትእዛዛት የተጻፉበት የቃል-ኪዳን ጽላት በርእሰ-አዲባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን





2ኛ ለዓለም ድኅነት ሲል በቀራንዮ አደባባይ መለኮታዊ ሕይወቱን የሠዋበት ግማደ-መስቀል (የመስቀሉ ቀኝ ክንፍ) በደብረ-ከርቤ ግሸን ማርያም

3ኛ. ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳላት ሥዕለ-አድኅኖ ወይም ፈዋሽ ስዕል እየተባለች የምትጠራው የእመቤታችን የቅድስተ-ቅዱሳን ድንግል ማርያም ስዕል በደብረ-ዘመዳ ገዳም



4ኛ. የሰብአዊውን ፍጡር ቅድመ-ታሪክ ያበሠረውና በዓለም አቀፍ ጠበብት የታሪክ ደረጃ የተሰጠው የሉሲ አጽም ዋናዋና ዎቹ ናቸው፡፡
(PhysOrg.com) -- Researchers at The University of Texas at Austin, in collaboration with the Ethiopian government, have completed the first high-resolution CT scan of the world's most famous fossil, Lucy, an ancient human ancestor who lived 3.2 million years

Read more at: http://phys.org/news153146616.html#jCp


ሌላው በማንም አገዛእ ሥር ያልወደቀች ክብሯንና ነጻነቷንና እምነቷን ጠብቃ የምተኖር የራሷ ፊደል፤አሃዝና ቋንቋ ያላት በቋንቋ በባሕል ልዩልዩ በሆኑ፤በፍቅር በሐገር አንድነትና በማሕበራዊ ኑሮ ግን እንደሰምና እንደወርቅ ተስማምተው በውሕደት ለጠላት በማይበገሩና የጋራ ክንዳቸውን በሚያነሱ የተወደዱ ብሔረ ሰቦች የተዋበች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር መሆኗ ነው፡፡ 

Ethiopia The Beautiful

ስለ ኢትዮጵያኛ ኢትዮጵያውያን ታላቅነት ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ ሳይሆኑ የሚናገሩት ታላላቅ የታሪክ ሰዎችና ቀደምት ፈላስፋዎች ጭምር ነቸው፡፡

ታላቁ የግርክ ባለቅኔ ሆሜርስ ኢትዮጵያውያን ሃያላን በመልክ የተደነቁና የሚማርክ ውበት ያላቸው ናቸው፡ በባሕርያቸውም ጭምቶችና ትሕትናን የተላበሱ ናቸው፤የ12ቱ የግሪክ አማልክተ አባት የሆነው ዜውስ የነዚህን ኃያላን ኢትዮጵያውያንን ውበት የማየት አብሮም ለመብላት ወደ ውቅያኖስ ወረደ፡ ሲል ከክርስቶስ ልደት በፊት በ5ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን መጨረሻ አካባቢ የነበረው ታላቁ የታሪክ አባት ሔሮዶቶስ ደግሞ በበኩሉ ኢትዮጵያውያን በቁመት፤በኃይልና በውበትም ከሁሉ የላቁ ናቸው በማለት መስክሯል፡፡ 

እንዲሁም ታላቁ የዓለም የሥነ-ጽሁፍ አባት ዊሊያም ሸክስፒር የጥቁርን ይልቁንም የኢትዮጵያዊን ውበት በታወቁት የፍቅር ግጥሞች ስብስቦቹ ለዛን በተመሉ ማራኪ ስንኞች አስውቦ ገልጦታል፡፡


ታዲያ ይህ ሁሉ ዓለም ያደነቀው ውበት የሥጋ ብቻ ሳይሆን የባህርይ ወይም የጠባይ፤ የእግዚአብሔር ጸጋና የመንፈሳዊነት ውበት ጭምር ነው፡፡

Thursday, June 12, 2014

እንኳን ደህና መጡ/ Welcome!

Welcome! and Thank you for visiting this blog. 

This Blog is still under construction please come back thank you again! 

"ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"

 ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለቺ ::መዝሙር 67፡31
"Ethiopia will stretch out her hands to God.."

"ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ዘንድ በተሰኘው በዚህ ድረ ገጽ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን እምነት፤ ባሕልና ትውፊት ሌሎችም ተጓዳኝ ትምህርቶች ባጭሩ እየተዘጋጁ ይቀርባሉ።

"EthiobyGod" Under this "EthiobyGod" blog, will be explored about the Ethiopia, Ethiopians,Ethiopian Languages, Cultures, Religions and Traditions, and much more!!



please visit the following

Andegna
Awde Tinat
Awde Tinat on youtube
Amazon
Facebook
My Poems Speak