Ethio by GOD/ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ዘንድ
"ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር" ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለቺ "Ethiopia will stretch out her hands to God.." መዝሙር 67፡31
Thursday, October 5, 2023
ልሳነ ግእዝ፡ የጋራ ቋንቋችን/Lisane Ge'ez: Yegara Quanquachin: LEGACY BY Tewolde G. Yohannes
ልሳነ ግእዝ፡ የጋራ ቋንቋችን/Lisane Ge'ez: Yegara Quanquachin: LEGACY BY Tewolde G. Yohannes: LEGACY BY Tewolde G. Yohannes A. LEGACY This is neither a sermon nor a term paper. So please read it carefully and try to understa...
Wednesday, March 24, 2021
Monday, February 1, 2021
Sunday, October 25, 2015
Tuesday, August 11, 2015
Saturday, July 19, 2014
Ethiopia The home-Land of God
ኢትዮጵያ ሐገረ -እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር አገር)
ነፍስ ካወቅንባት ቅጽበት ጀምሮ በጆሯችን እንደ ጠገብነው ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር፤ የሃይማኖት
መዲና፤ ወይም ማዕከል ትባላለች፤እውነትም ናት፡፡ ከሥጋዊ ድሃነቷ ወይም ችግረኛነቷ ጋር እንኳን እምነቷ አይዛባም፡፡ እግዚአብሔር
ጸጋውን አድሏታል፡፡
የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆነው የመጻህፍት ሁሉ አባት መጽሐፍ ቅዱስ እንኳ “ኢትዮጵያ” ወይም ኩሽ የሚለውን ቃል ወይም ስም በ17 የመጽሐፍ ቅደስ ክፍልች 47 ጊዜ
ጠቅሶት ይገኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያተኩርባቸው አበይት ነጥቦች
መካከልም መልክኣ ምድሯ፤ እምነቷ፤ ደግነትዋና ከእግዚአብሔር ጋር ያላት ጽኑ ፍቅር ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ስለኢትዮጵያ ታላቅነት፤ ስለሕዝቧ ዕፁብ ድንቅ ተፈጥሮ፤ባህልና ጠባይ እንዲሁም ትሕትናና እምነትን
የተላበሰ አስተዋይነት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን የዓለማችን ታላላቅ ጠበብትም ብዙ ተናግረዋል፡፡ከብዙዎቹም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል
ከክርስቶስ በፊት በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ታላቁ የግሪክ ባለቅኔ ሆሜር ‹‹ ኢትዮጵያውያን በጉልበት ኃያላን፤
በመልክ የተደነቁ፤ በውበት የተዋቡ፤በጠባያቸውም ትሕትናን የተላበሱ አስተዋዮች ናቸው›› ሲል የምዕራቡ ዓለም የታሪክ
አባት እየተባለ የሚጠራው ሔሮዶቶስ በበኩሉ ‹‹ ኢትዮጵያውያን በውበት፤ በቁመትና በኃይል የተለዩ፤ የተደነቁም ናቸው››
ብሏል፡፡
እንዲሁም ታላቁ የዓለም የሥነ-ጽሁፍ አባት የሆነው እንግሊዛዊው ዊሊያም ሸክስፒር ኢትዮጵያውያን ማራኪና
በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ውበት የታደሉ ውቦች መሆናቸውን ማራኪና ውብ በሆኑት በታወቁት የፍቅር ግጥሞቹ ወይም ቅኔዎቹ አሳምሮ
ገልጦታል፡፡ ሲሉ የታሪክ ጸሐፊዎች መዝግበውት ይገኛሉ።
ታዲያ ይህ ሁሉ ዓለምን የሳበው ውበት በደረቁ ሥጋዊ ውበት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ጸጋም ጭምር ስለተዋሐደው
ነው፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተለየ ፍቅር እንደ ሚወዳቸው ወይም እንደ ሚወደን በቃል ብቻ ተወስኖ
ወይም በመጻሕፍት ብቻ ተመዝግቦ አልቀረም፡፡
ነገር ግን ተጨባጭ የሆነና ከዓለም የተለየ ክብርና መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ዝናን ከነሙሉ
ታሪኩ አጎናጽፎናል፡፡ ይህ እውነተኛ ፍቅር ከተገለጠባቸው መካከልም የሚከተሉት ዓለም አቀፍ የታሪክና የእምነት ቅርሶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
እነዚህም

2ኛ. ለዓለም ድኅነት ሲል በቀራንዮ አደባባይ መለኮታዊ
ሕይወቱን የሠዋበት ግማደ መስቀል (የመስቀሉ ቀኝ ክንፍ ወይም ክፍል) በደብረ-ከርቤ ግሸን ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ
የሚገኝ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዐፄ ዳዊት ጊዜ በአቡነ ዮሐንስ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አማካኝነት
ነው፡፡
3ኛ. ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳላት
የመጀመሪያዋ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል (ምስለ ፍቁር ወልዳ) ወይም ስዕለ አድኅኖ
(ፈዋሽ ስዕል) በደብረ ዘመዳ ገዳም የምትገኝ ሲሆን ወደ ዚህ ገዳም (ወደ ኢትዮጵያ) የገባቺው በ14ኛው መቶ ክፍለ
ዘመን በዐፄ ዳዊት ጊዜ በአቡነ ዮሐንስ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አማካኝነት ከግማደ መስቀሉ ጋር እንደ ነበረ ታሪክ ይናገራል፡፡
4ኛ. የሰብአዊውን ፍጡር ቅድመ ታሪክ ያበሠረውና በዓለም
አቀፍ ጠበብት የታሪክ ደረጃ የተሰጠው የሉሲ ወይም በኢትዮጵያዊ ስሟ የድንቅነሽ አጽም በ1974 ዓ/ም ከከርሰ
ምድር ውስጥ የተገኘው እውነት ነው፡፡
እነዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ጥቂቶቹ ሲሆኑ ሌላው ታላቁ ስጦታዋ ደግሞ በማንም አገዛዝ ሥር ያልወደቀች፤ በምታምነውና በሚወዳት በልዑል እግዚአብሔር ኃይል ተጠብቃ የምትኖር፤የራሷ ፊደል፤ቋንቋ፤አኃዝ፤ዕፁብ
ድንቅ የሆነ ባህልና የሥነ-ጽሁፍ ስልት ያላት ብቼኛዋ አፍሪካዊት አገር መሆኗ ነው፡፡
To watch video please click this
To watch video please click this
Sunday, June 15, 2014
The Grace of Ethiopia
እግዚአብሔር
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተለየ ፍቅር እንደሚወደን በቃል ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡ ከዓለም የተለየ ክብርና ታሪክ
አጎናጽፎናል፡፡ ይህም በሚከተሉት ዓለም አቀፍ የታሪክና የእምነት ቅርሶች ሊገለጽ ይችላል፡፡ከነዚህም መካከለል
ኢትዮጵያዊው ዶ/ር
ቶሎሣ እንደሌለ ያስተባበሉት ግን እውነት እውነት እንጂ ሌላ ስም ስለማይኖረው ትርፉ ትዝብት ይልቁንም ቅሌት ብቻ ነው፡፡
2ኛ ለዓለም ድኅነት ሲል በቀራንዮ አደባባይ መለኮታዊ ሕይወቱን
የሠዋበት ግማደ-መስቀል (የመስቀሉ ቀኝ ክንፍ) በደብረ-ከርቤ ግሸን ማርያም
3ኛ. ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳላት
ሥዕለ-አድኅኖ ወይም ፈዋሽ ስዕል እየተባለች የምትጠራው የእመቤታችን የቅድስተ-ቅዱሳን ድንግል ማርያም ስዕል
በደብረ-ዘመዳ ገዳም
4ኛ. የሰብአዊውን ፍጡር ቅድመ-ታሪክ ያበሠረውና
በዓለም አቀፍ ጠበብት የታሪክ ደረጃ የተሰጠው የሉሲ አጽም ዋናዋና ዎቹ ናቸው፡፡
![]() |
(PhysOrg.com) -- Researchers at The University of Texas at Austin, in collaboration with the Ethiopian government, have completed the first high-resolution CT scan of the world's most famous fossil, Lucy, an ancient human ancestor who lived 3.2 million years Read more at: http://phys.org/news153146616.html#jCp |
Subscribe to:
Posts (Atom)